#ትማርኢትዮጵያ
በሀገር አቀፍ ፈተና ውጤታችሁ የሰመረላችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። በርካቶች እነዚህን ወጣቶች እንድንደግፍ ለትማር ኢትዮጵያ ጥሪ ስታደርጉ ነበር። እነሆኝ ብለናል። እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አቅም ያላቸውን ወጣቶች ለማስተርስና PhD ማመልከቻ ዝግጅት እንዲያደርጉ ለማገዝ ተገኝተናል።
በዚህም መሠረት በመነሻነት
5 በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ
5 በማስተርስና በPhD ውጭ ሀገር መማር ለሚፈልጉ...
አሜሪካን ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፕሮፌሰሮች ጋር በመተባበር... በነፃ የማማከር አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅተናል። በዚህም ልጆቻችን እንዴት የተሻለ እድልና አማራጭ ማግኘት እንደሚችሉ፣ ምን አይነት አማራጮች እንዳሏቸው እናመላክታለን።
አስፈላጊ የትምህርት ውጤት ዶክመንት፣ አጭር Personal Letterና የቋንቋ አቅሜን ያሳይልኛል የምትሉትን ፈተና ወይንም ውጤት አያይዛችሁ በሊንክዲን የውስጥ መልእክት አልያም በትማር ኢትዮጵያ ይፋዊ ድረ ገጽ https://timarethiopia.org/contact በመግባት መጎብኘትና ኢሜል በማድረግ ልታደርሱን ትችላላችሁ።
ሌሎቻችሁ ይሄ እድል ይገባቸዋል ለምትሉና ተማሪዎችና ወላጆቻቸው በማጋራት አድርሷቸው።
ማመልከቻ ቀናት (29/08/2026 - 02/09/2026)
Categories: Scholarships
ASCHALEW ABUYE
2 days agoThank you Mr mitiku kebede this great opportunity for Us Gos bless you
dejene Desse
2 days agoHow to apply for the Ms and pH
elsa ajebew
22 hours agoHow apply this chance